消息详情
ተግባራዊ ክርስትና · @Applied_CHRISTIANITY · 2026年11月6日 17:31
📖 የመድኃኔዓለም ሞቱን ታዩ ዘንድ ኑ ! ወዮ ! ለዚህ ለመድኃኔዓለም ፍጹም ትዕግስት አንክሮ ይገባል ። በመድኃኔዓለም ክርስቶስ ሞት በአንድነት እናለቅስ ዘንድ ቅዱሳን ሁላችሁ ኑ ! መድኃኒታችን ሙቷልና ፍጥረታት ሁሉ ያለቅሳሉ ፤ መያዝንና መታሠርን የተቀበለ መድኃኒታችን ሙቷልና ፡፡ ጥፊንና ግርፋትን የተቀበለ መድኃኒታችን ሞተ ፡፡ መደብደብንና መመታትን የታገሰ መድኃኒታችን ሞተ ፡፡ ሄኖክ ፡ እግዚአብሔር ‹‹በሴም ቤት ይደር›› ብሎ አብ ስለራሱ የተናገረለት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና ፡፡ አብርሃም ፡ ቃልኪዳን የገባልህን የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና ፡፡ ይስሐቅ ፡ ከሰይፍ ቤዛ የሆነህን የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና ፡፡ ያዕቆብ ፡ በበረሃ የታገለህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና ፡፡ ኢዮብ ፡ በደመና የታየህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና ፡፡ሙሴ ፡ ስለ እርሱ ‹እንደእኔ ያለ ነቢይ ይነሣል› ብለህ የተናገርኽለት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና ፡፡ ዳዊት ፡ ‹‹እነሆ በኤፍራታ ሰማነው፣ በበረሃ ዛፍም አገኘነው›› ብለህ የተናገርኽለት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና ፡፡ ኤርሚያስ ፡ ‹‹የክቡሩን ዋጋ ሠላሳ ብር ተቀበሉ›› ብለህ የተናገርኽለት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና ፡፡ ኢሳይያስ ፡ ‹‹ወልድ ሰው ለመሆን ተገለጠልን፣ ሕፃን ተወለደልን፣ ድንቅ መካር ኃያል አምላክ›› ብለህ የተናገርኽለት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና ፡፡ ሕዝቅኤል ፡ ‹‹አምላክ ወደ ተዘጋች ደጃፍ ገባ፣ ከተዘጋች በርም ወጣ›› ብለህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና ፡፡ ዳንኤል ፡ ነጭ ሐር ለብሶ ያየኸውን የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና ፡፡ ኤልያስ ፡ ከሞት በፊት የሰወረህ በእሳት ፈረሶች ያሳረገህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና ፡፡ ሕዝቅያስ ፡ የፀሐይ መግባቱን ያሳየህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና ፡፡ ምናሴ ፡ ችንካሮችህን ከእግር ብረት የፈታ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና ፡፡ ኢዮስያስ ፡ ፋሲካውን ያደረግህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና ፡፡ አናንያ ፣ አዛርያ እና ሚሳኤል ፡ ከእሳት ምድጃ ያዳናች የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ኑ ፡፡ አብያና ሲላ ፡ ፌንቶስ ከመወለዱ አስቀድሞ ያመናችሁበት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ኑ ፡፡ የቀድሞ አባቶች ነቢያት ሁላችሁ ከፋራን ተራራና ከቴማን ይመጣል ያላችሁት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ኑ ፡፡ አሞፅ ፡ በአድማስ ቅጥር ያየኸው የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና ፡፡ ዘካርያስ ፡ በተራራዎች መካከል ያየኸው የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና ፡፡ ዕዝራ ፡ በአርፋድ በረሃ ያየኸው የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና ፡፡ ስምዖን ፡ በክንድህ የታቀፍከውን ሕፃን የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና ፡፡ ዮሴፍ ፡ እንደ አንተ የተሸጠ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና ፡፡ ጠራቢ ዮሴፍ ፡ በትከሻህ ያዘልከው በክንድህ የተሸከምከው ሕፃን የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና ፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ ፡ ከሕፃንነትህ ጀምሮ በበረሃ ያለ እናት ያለ አባት ያሳደገህ መንገዱንም እንድትጠርግለት ያዘጋጀህና መለኮትን እንድታጠምቅ የመረጠህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና ፡፡ ኢያቄምና ሐና ሆይ ፡ የልጃችሁን ልቅሶዋን የልቧንም መዘንጋት ታዩ ዘንድ ኑ ፡፡ ከሔዋን እስከ ፋኑኤል ልጅ እስከ ሐና ፡ ያላችሁ ሁላችሁ ቅዱሳት ሴቶች የድንግልን ልቅሶዋን ታዩ ዘንድ ኑ ፣ አንድ ልጇ ሙቷልና ፡፡ 🔴 ዛሬ ማታ Live ትምህርት አይኖረንም !
相關消訊
- JOIN @Applied_CHRISTIANITY
- "..... ዓለምን በመዳፉ የያዘ አምላክ በአይሁድ እጅ እንደ ሌባ ተያዘ ፡፡ ሠራዊተ መላእክት ለምሥጋና በፊቱ የሚቆሙለት መድ…
- ✝️ ካየሁት እና ከሰማሁት 👀 +👂 ❖ ክፍል 1 ..... ታክሲ ውስጥ ሆኜ ሁለት ሰዎች ሲያወሩ እሰማለሁ ። ርዕሳቸው ስለ …
- ✝️ እግዚአብሔር አለ ! ❖ ክፍል ፪/2 « ሰነፍ በልቡ ፥ « "እግዚአብሔር የለም" ይላል ። » /መዝ ፩፫÷፩/ በዚህ …
- ✝️ እግዚአብሔር አለ ! ❖ ክፍል ፩ /1 « ሰነፍ በልቡ ፥ « "እግዚአብሔር የለም" ይላል ። በሥራቸው ረከሱ ፣ ጎሰቆሉ…
- "በእውኑ እኛ ነን እግዚአብሔር የረሳነው ወይስ እርሱ ነው የረሳን ?"
- ኢሳይያስ 49÷15: "በውኑ ሴት ከማኅፀንዋ ለተወለደው ልጅ እስከማትራራ ድረስ ሕፃንዋን ትረሳ ዘንድ ትችላለችን? አዎን፥ እር…
- ኑ ትምህርት ጀምረናል !
- ከ10 ደቂቃ በኋላ እንጀምራለን ! ዝግጁ ሁናችሁ ጠብቁ ።
- የዳዊት መዝሙር ፲፫÷፩-፯ "ሰነፍ በልቡ ፡ «እግዚአብሔር የለም» ይላል ። በሥራቸው ረከሱ ፣ ጎሰቆሉም በጎ ነገርን የሚሠራ…