選擇語言
繁體中文
繁體中文 Traditional Chinese
简体中文
简体中文 Simplified Chinese
English
English English
日本語
日本語 Japanese
AI 助手

今日情報速問。不用選範圍,直接問今天值得看什麼。

完整分析

通知訊訊

暫無新訊訊

✝️ እግዚአብሔር አለ ! ❖ ክፍል ፪/2 « ሰነፍ በልቡ ፥ « "እግዚአብሔር የለም" ይላል ። » /መዝ ፩፫÷፩/ በዚህ ዘመን በክርስቲያኖች ላይ መከራ ሲበዛ ስንመለከት እግዚአብሔር የተወን ይመስለናል ነገር ግን እግዚአብሔር አለ አልተወንም ። እግዚአብሔር ያለ ብቻ ሳይኖር ለዘለዓለም የሚኖር ነው ። የዚህ ዓለም ወዳጅነት ያለ ጥቅም አይቆምም እግዚአብሔር ግን ያለ ጥቅም እንዲሁ ይወደናል ። እግዚአብሔር ይህንን መከራ እንድናይ የተወን የዓለምን ጠባይ እንድንረዳ ፣ ክፉ የሆነውን ከደጉ እንድንለይ ነው ። ከእርሱ ውጪ ነገሥታትን ፣ ዓለምን ተስፋ ብናደርግ ጥቅም አልባ እንደሆነ ሊያሳየን ዝም ይለናል ። አንድ አባት "የለህም እንዳልል ይመሻል ይነጋል ፤ አለህም እንዳልል ይህ ሁሉ ይደረጋል" ብለዋል ። መሽቶ መንጋቱም የእግዚአብሔር ምሕረት ነው ። ጠላት ዲያቢሎስ የእኛ መኖር ያንገበግበዋል በዚህም ምክንያት የሞት ድግስ ያዘጋጅልናል ። የክርስቲያኖች መከራ ዛሬ የጀመረ አይደለም ። እግዚአብሔርን የተጠጋ ሰው ደሙ መፍሰስ የጀመረው ገና ዛሬ አይደለም ። ቃኤል ወንድሙ አቤልን የገደለው ከዛሬ 7ሺ ዓመት በፊት ነው ። አይነቱና ቦታው ይለያይ እንጂ በየዘመኑ ሰማዕትነት አለ ። ጌታችንም ለደቀ መዛሙርቱ ስለ ዓለም መጨረሻ በተናገረበት አንቀጽ "በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችኋል ይገድሉአችሁማል ፥ ስለ ስሜም በአሕዛብ ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ ። በዚያን ጊዜም ብዙዎች ይሰናከላሉ እርስ በርሳቸውም አሳልፈው ይሰጣጣሉ እርስ በርሳቸውም ይጣላሉ ። /ማቴ 24÷9-10/ ብሎናል ። ሰነፍ ግን ይህን ሁሉ እያወቀ በልቡ እግዚአብሔር የለም ይላል ። ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ይጠብቀን ! . . ..... ይቀጥላል !