消息详情
ተግባራዊ ክርስትና · @Applied_CHRISTIANITY · 2026年11月4日 17:31
✝️ ካየሁት እና ከሰማሁት 👀 +👂 ❖ ክፍል 1 ..... ታክሲ ውስጥ ሆኜ ሁለት ሰዎች ሲያወሩ እሰማለሁ ። ርዕሳቸው ስለ ፈጣሪ መኖርና በዙሪያችን ስለሚፈጠሩ ምድራዊ ችግሮች ነው ። አንደኛው " እኔ እግዚአብሔር አለ ብዬ ለመቀበል እቸገራለው ምክንያቱም ይህ ሁሉ ረሃብ ፣ ጦርነት እያለ ዝም ብሎ የሚመለከት አምላክ አለ ብሎ ለመቀበል ይቸግረኛል ።" ሲል ! ጓደኛው ቀበል አድርጎ "ፈጣሪን ተወውና አንተስ ምን አደረግክ ?" አለው ። እኔም በጓደኛው መልስ በጣም ተገርሜ በልቤ ይህን አሰብኩ ፦ እ ! ..... አስተውላችሁ ከሆነ ! አብዛኛውን ጊዜ የዓለምን ክፋትና ጉድለት ስንመለከት ጣታችንን ወደ ሰማይ መቀሰር ያምረናል ። "ለምን ጦርነት ይሆናል? ለምን ረሃብ ይበረታል?" እንላለን ። ነገር ግን ጦርነቱን የሚጭረው ፣ ረሃቡንም የሚያመጣው ፣ ጥላቻውን የሚዘራው ራሱ ሰው መሆኑን እንዘነጋዋለን ። እግዚአብሔር ሰውን ማሽን አድርጎ አልፈጠረውም ፤ የራሱ ምርጫና ነፃነት (Free Will) ሰጥቶታል ። ዓለም የምትበላሸው ፈጣሪ ስለሌለ ሳይሆን ፣ ሰው የተሰጠውን ነፃነት ለጥፋት ስለተጠቀመበት ነው ። ዓለም እንድትቀየር ከፈለግን "ፈጣሪ ለምን ዝም ይላል?" ከማለት ይልቅ "እኔ በበኩሌ ምን እያደረግኩ ነው?" ወደሚለው ጥያቄ መዞር አለብን ። በረሃብ ለሚሰቃይ ሰው አንተ አንድ እንጀራ ስትሰጥ እግዚአብሔር መኖሩ በአንተ በኩል ይታወቃል ፣ በአንተ ምክንያት ቸሩ መድኀኔዓለም ይመሰገናል /ማቴ 5÷16/ ። ልክ እንደዚሁ ለቤተ ክርስቲያን ጥፋትም የእግዚአብሔርን ዝምታ ፣ የካህናትን ኃጢአት እያየን ለምንሰናከል ሁሉ መልእክቱ ለእኛም ነው ። ..... "እኔስ ምን እያደረኩ ነው ?" በሉ ! #ጥቅምት 25 ቀን 2019 ዓ.ም
相關消訊
- JOIN @Applied_CHRISTIANITY
- "..... ዓለምን በመዳፉ የያዘ አምላክ በአይሁድ እጅ እንደ ሌባ ተያዘ ፡፡ ሠራዊተ መላእክት ለምሥጋና በፊቱ የሚቆሙለት መድ…
- ✝️ እግዚአብሔር አለ ! ❖ ክፍል ፪/2 « ሰነፍ በልቡ ፥ « "እግዚአብሔር የለም" ይላል ። » /መዝ ፩፫÷፩/ በዚህ …
- ✝️ እግዚአብሔር አለ ! ❖ ክፍል ፩ /1 « ሰነፍ በልቡ ፥ « "እግዚአብሔር የለም" ይላል ። በሥራቸው ረከሱ ፣ ጎሰቆሉ…
- "በእውኑ እኛ ነን እግዚአብሔር የረሳነው ወይስ እርሱ ነው የረሳን ?"
- ኢሳይያስ 49÷15: "በውኑ ሴት ከማኅፀንዋ ለተወለደው ልጅ እስከማትራራ ድረስ ሕፃንዋን ትረሳ ዘንድ ትችላለችን? አዎን፥ እር…
- ኑ ትምህርት ጀምረናል !
- ከ10 ደቂቃ በኋላ እንጀምራለን ! ዝግጁ ሁናችሁ ጠብቁ ።
- የዳዊት መዝሙር ፲፫÷፩-፯ "ሰነፍ በልቡ ፡ «እግዚአብሔር የለም» ይላል ። በሥራቸው ረከሱ ፣ ጎሰቆሉም በጎ ነገርን የሚሠራ…
- ✝️ በመልካም አስበኝ ! ጠላቴ ሰይጣን በክፉ ሲያስበኝ አንተ ግን በመልካም አስበኝ ። በፈረሰው ከማዝን የፈረሰውን እሠራ ዘ…