消息详情
ተግባራዊ ክርስትና · @Applied_CHRISTIANITY · 2026年11月1日 18:08
✝️ እግዚአብሔር አለ ! ❖ ክፍል ፩ /1 « ሰነፍ በልቡ ፥ « "እግዚአብሔር የለም" ይላል ። በሥራቸው ረከሱ ፣ ጎሰቆሉም በጎ ነገርን የሚሠራ የለም ። እንድም እንኳ የለም ። » /መዝ ፩፫÷፩/ በዘመናችን የምንሰማቸው ነገሮች እግዚአብሔር እንደሌለ ያስመስላሉ ። ስለዚህ እግዚአብሔር አለ የሚለው ስብከት ሊሰበክ ይገባዋል ። እግዚአብሔር አለ የሚለው ስብከት ለማያምኑ (አሕዛብ) ብቻ የሚሰብከ አይደለም ። እግዚአብሔር አለ የሚለው ስብከት በቤቱ ውስጥ ግራ ተጋብተን ለተቀመጥን ለእኛም ሊሰበክ ይገባዋል ። እግዚአብሔር አምላክ ትናንት የነበረ ዛሬም ያለ ነገም የሚኖር ነው ። ነገር ግን ሰነፍ በልቡ "እግዚአብሔር የለም" ይላል ። ባለፉት ዘመናት በአደባባይ እግዚአብሔር የለም ይባል ነበር ። ወላጆች ልጆቻቸውን ክርስትና ለማስነሳት እንኳ እስኪቸገሩ ድረስ ጭንቅ ነበር ። በጊዜው ስለ እግዚአብሔር መኖር ያስተምሩ የነበሩ ሊቃውንት ዝም ሲሉ ከሥራቸው ይማሩ የነበሩ ምዕመናን ግን በአደባባይ "እግዚአብሔር አለ" ብለው መስክረው ሰማዕትነት ተቀብለዋል ። እንዳንዶችም ዘመኑ ክፉ ነው ብለው በአፋቸው ክደው በልባቸው አምነዋል ። ወገኖቼ የመከራ ቀን መጥቶ እንኳ "እግዚአብሔር የለም" ብለን ብንክድ እርሱ ዝም አይለንም እንደ ጴጥሮስ ሆነናልና ያዝንብናል ። "ሰነፍ በልቡ እግዚአብሔር የለም ይላል ።" ..... ይቀጥላል !
相關消訊
- አማኑኤል አምላኬ ሆይ ! ስለ ቀደሙ ቅዱሳን አባቶቻችን ብለህ እባክህ በምሕረት ተመልከተን !
- 📖 የመድኃኔዓለም ሞቱን ታዩ ዘንድ ኑ ! ወዮ ! ለዚህ ለመድኃኔዓለም ፍጹም ትዕግስት …
- JOIN @Applied_CHRISTIANITY
- "..... ዓለምን በመዳፉ የያዘ አምላክ በአይሁድ እጅ እንደ ሌባ ተያዘ ፡፡ ሠራዊተ መላእክት ለምሥጋና በፊቱ የሚቆሙለት መድ…
- ✝️ ካየሁት እና ከሰማሁት 👀 +👂 ❖ ክፍል 1 ..... ታክሲ ውስጥ ሆኜ ሁለት ሰዎች ሲያወሩ እሰማለሁ ። ርዕሳቸው ስለ …
- ✝️ እግዚአብሔር አለ ! ❖ ክፍል ፪/2 « ሰነፍ በልቡ ፥ « "እግዚአብሔር የለም" ይላል ። » /መዝ ፩፫÷፩/ በዚህ …
- "በእውኑ እኛ ነን እግዚአብሔር የረሳነው ወይስ እርሱ ነው የረሳን ?"
- ኢሳይያስ 49÷15: "በውኑ ሴት ከማኅፀንዋ ለተወለደው ልጅ እስከማትራራ ድረስ ሕፃንዋን ትረሳ ዘንድ ትችላለችን? አዎን፥ እር…
- ኑ ትምህርት ጀምረናል !
- ከ10 ደቂቃ በኋላ እንጀምራለን ! ዝግጁ ሁናችሁ ጠብቁ ።