消息详情
ተግባራዊ ክርስትና · @Applied_CHRISTIANITY · 2026年11月19日 22:22
✝️ ሊቀ ጳጳሱ በቃለ መጠይቁ ላይ ፦ ፨ 195 ዓመት ዕድሜ የሆነው ቤተ ክርስቲያን አሁን ጫት መቃሚያ ሆኖ ቀርቷል፣ እዚያ መሄድ አይቻልም ፣ ሌላው በሰላም ይገባል ይወጣል፣ ልጆቻችን (ኦርቶዶክሳውያኑ) ግን መግባት መውጣት አይችሉም፣ ጥቃትም ደርሶ መረጃ እንዳይወጣ ይከለክሉ ነበር፣ ለቀብር የሄዱ እና የቀበሩ ለእስር ይዳረጉ ነበር፣ ለምን እዚህ ጋር ተገኛችሁ ብለው ነበር ያሰሯቸው፣ ዞሮ ተፈተዋል ፡፡ ፨ ጥቅምት 14 ቀን 2019 ዓ.ም ቅዳሜ ዕለት በጽርሐ አርያም ቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን የሚኖሩ ልጆቻችን የፖለቲካ ሰዎች አይደሉም የሰላም ሰዎች የሆኑ ሌሊቱን ሙሉ አካባቢያቸውን ሲጠብቁ አድረው ጧት ላይ ሰላም ነው ብለው ወደ ቤት ሲገቡ ሦስት እነመ አራት ሺህ የሚሆኑ ናቸው ጠላት በዚያ ልክ በአራት ማዕዝን ተኩስ ጠምዶባቸው በአንድ ቀን ብቻ 43 ክርስቲያኖች ተገደሉ ቀብሩ ላይ ያየነው በአንድ ጉድጓድ ሲቀበሩ ነው ፡፡ ፨ እዚያ ስንደርስ ምዕመኑ በልቅሶ ነው የተቀበለን ፣ የደረሰልን የለም ፣ በዓላማ እየሞትን ፣ እየተገደልን ነው ፣ አረዱን ፣ አቃጠሉን እያሉ ነው በዋይታ የተቀበሉን ፡፡ ያልተደረገብን ፣ ያልደረሰብን ጥቃት የለም ፣ በቁማችን ነው የገደሉን ፣ 2016 ዐመተ ምሕረት መስከረም ወር "አንዲት እናት ወልዳ ሰባ ቀን ሆኗት ከነልጇ ነው ያረዷት ፣ ሁለት አባዎራዎች በአንድ ቤት ውስጥ እያሉ ነው ያቃጠሏቸው ፣ አጽማቸውን ከሁለት ወራት በኋላ በማዳበሪያ ሰብስበን ነው የቀበርነው" አሉኝ ካህናቱ ፣ ይቺ ቤተ ክርስቲያን ምን እንዳደረገች አናውቅም ! "አንተ የምትተኛ ንቃ !" /ኤፌ 5÷14/
相關消訊
- 📖 ይዘነጋል ! JOIN @Applied_CHRISTIANITY
- አይሁድ በጌታችን ራስ ላይ ያኖሩት የሚያደማ እሾህ ዛሬም በክርስቲያኖች ራስ ላይ አለ ። ይህን እሾህ በጌታችን ክርስቶስ ራስ …
- "..... በየቦታው የሚደረጉ ጥቃቶች በሚገባ በመንግሥት መዋቅር የሚደረጉ ናቸው ። በአርሲ ፣ በባሌ ፣ በጂማ... ሕዝቡን ሊ…
- 📖 መሠረታዊ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት PDF ❖ ምዕራፍ ፩/1 ..... ትምህርተ ሃይማኖት ❖ ምዕራፍ ፪/2 ..... አምስ…
- ✝️ አጭር መልእክት ፡- "" ስለ ሳምንታዊ መርሐ ግብር "" #ኅዳር 8 ቀን 2019 ዓ.ም
- ✝️ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✝️ ❖ ሰላም ለእናንተ ይሁን ! በቻናላችን ላይ አስተያየት …
- 📖 ኑ ከድንግል ማርያም ጋር አብረን እንሰደድ ! "..... ይኽ ድንቅ ምሥጢርን የያዘው ድርሰት አምላክን በድንልና የወለደች…
- ✝️ ቁስቋም [ ኅዳር 6 ] ኅዳር 6 ቀን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተወደደ ልጇን አዝላ ወደ ግብጽ የተሰደደችበት…
- ✝️ እውነት ለመናገር ጉዳዩን ስመለከት የምለው ጠፍቶኝ ነበር ይህ ግሩም የሆነ ምላሽ ነው !
- #ሼር 📎 ለኦርቶዶክሳውያን ሁሉ ይድረስ ፡- https://t.me/Applied_CHRISTIANITY