消息详情
ተግባራዊ ክርስትና · @Applied_CHRISTIANITY · 2026年11月15日 00:52
✝️ ቁስቋም [ ኅዳር 6 ] ኅዳር 6 ቀን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተወደደ ልጇን አዝላ ወደ ግብጽ የተሰደደችበት ስደት የተፈጸበት ቀን ነው ። ደብረ ቁስቋም በደቡብ ግብፅ የሚገኝ ተራራ ነው ። ደብረ ቁስቋም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲሁም ቅዱስ ዮሴፍና ቅድስት ሰሎሜን ይዛ ከስደት ሲመለሱ ያረፋበት ቦታ ነው ። እመቤታችን ከተወደደ ልጇ ጋር በደብረ ቁስቋም ገብተው ካገኛቸው ድካም ባረፉበት በዚሁ ቀን የጌታ መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ታይቶ "የሕፃኑን ነፍስ የፈለጉት ሞተዋልና ተነሣ ፥ ሕፃኑን እናቱንም ይዘህ ወደ እስራኤል አገር ኺድ"ብሎታል ። /ማቴ 2፥19-20/ በነገረውም መሰረት እናቱንና ሕፃኑን ይዞ ተመልሷል ። ከግብጽ ሲመለሱም ጌታችን በእመቤታችን ጀረባ ላይ ሆኖ ድውያንን በፈወሱ ጣቶቹ ወደ ኢትዮጵያ ይጠቁም ያመለክት ነበር፤ እመቤታችንም "ልጄ ሆይ ለምንድነው ጣትህን የምታመለክተው?" ብትለው "ያቺ የተባረከች አገር ናት እኔን የሚያመልኩ አንቺን የሚማልዱ በፍቅርሽ የነደዱ ቅዱሳን መነኮሳት የሚፈልቁባት አገር ናት፤ ያንቺ ዘመዶች ሰቅለው ይገድሉኛል በዚህች አገር ያሉ ግን ሳይዩኝ ያመኑኛል፤ አስራት ሀገርሽ ትሁን" ብሎ ሰጥቷታል ። በኪደተ እግራቸውም ጣና ሐይቅን፣ ዋልድባንና ሌሎችንም ቦታዎች ዞረው እንደባረኩ ድርሳነ ዑራኤልና ተአምረ ማርያም ላይ በስፋት ተጽፏል ። "የዓለም ፡ ሁሉ ፡ እመቤት ፡ ሆይ ፡ ልመናችንን ፡ ትሰሚ ፡ ዘንድ ፣ ከኀዘናችንም ፡ ታረጋጊን ፡ ዘንድ ፡ ወደኛ ፡ ነይ ፡፡"
相關消訊
- 📖 ይዘነጋል ! JOIN @Applied_CHRISTIANITY
- ✝️ ሊቀ ጳጳሱ በቃለ መጠይቁ ላይ ፦ ፨ 195 ዓመት ዕድሜ የሆነው ቤተ ክርስቲያን አሁን ጫት መቃሚያ ሆኖ ቀርቷል፣ እዚያ …
- አይሁድ በጌታችን ራስ ላይ ያኖሩት የሚያደማ እሾህ ዛሬም በክርስቲያኖች ራስ ላይ አለ ። ይህን እሾህ በጌታችን ክርስቶስ ራስ …
- "..... በየቦታው የሚደረጉ ጥቃቶች በሚገባ በመንግሥት መዋቅር የሚደረጉ ናቸው ። በአርሲ ፣ በባሌ ፣ በጂማ... ሕዝቡን ሊ…
- 📖 መሠረታዊ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት PDF ❖ ምዕራፍ ፩/1 ..... ትምህርተ ሃይማኖት ❖ ምዕራፍ ፪/2 ..... አምስ…
- ✝️ አጭር መልእክት ፡- "" ስለ ሳምንታዊ መርሐ ግብር "" #ኅዳር 8 ቀን 2019 ዓ.ም
- ✝️ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✝️ ❖ ሰላም ለእናንተ ይሁን ! በቻናላችን ላይ አስተያየት …
- 📖 ኑ ከድንግል ማርያም ጋር አብረን እንሰደድ ! "..... ይኽ ድንቅ ምሥጢርን የያዘው ድርሰት አምላክን በድንልና የወለደች…
- ✝️ እውነት ለመናገር ጉዳዩን ስመለከት የምለው ጠፍቶኝ ነበር ይህ ግሩም የሆነ ምላሽ ነው !
- #ሼር 📎 ለኦርቶዶክሳውያን ሁሉ ይድረስ ፡- https://t.me/Applied_CHRISTIANITY